Telegram Group Search
ስለ እናት pinned «☞☞☞ ማን ያውቃል☜ ☜☜ ዛሬም እንደ ትላንት ተረስቶ ነበር ከሆነ የትላንት ሁኔታ ለዛሬ ትውስታ ለነገ ህልምታ ወይም ትዝታ አልያም በሽታ ከሆነ የትላንቱ ፍቅር ዛሬ ካልፀደቀ ትላንት ፈንድቶ ትላንት ከደረቀ ወይም ትላንትን ጥሎ በትላንት ህልም ዛሬ ከወደቀ አልያ ትላንት አክብሮ በዛሬ ተናፍቆ ለነገ ትዝታ ከሆነ ማን ያውቃል የዛሬው ዛሬዬ ነገን ካረገዘ ናፍቆቴም ትዝታን ከወለደ በዚህ ማሃል ማን…»
ሁላችሁም እንዴት ናችሁ
አድዋን የመድረክ ስራ ለመስራት ሽር ጉዱን ይዘነዋል ነገር የሚጥም ከወዳጅ ጋር ነውና ወዳጆች ሆይ የኛ የሆነውን እኛው እንስራው እናሙቀው እንደግሰው ብለን መቅድሙን ለናንተ አቀበልናችሁ

በትወናውም
በሽለላውም
በድምፁም
በአጀብም



ተወዳጆቼ ሠንዳ ሠንዳ ዘግጀት ዘግጀትጀት እርግፍ እርግፍ ብላችሁ ጠብቁኝ ነገ አልያ ተነገ በስቲያ መገናኛችንን ቆርጠን በአይነ ስጋ ተገናኝተን ነገሩን ነገሬ ብለን እንመክርበታለን !
ደግ ሠንብቱኝማ
ታውቁም አደል እወዳችኋለሁ
ሞቅ በሉልኝ

@Seblye_production
ስለኖርነው ሁሉ ምስጋናን ልናደርግ ወደድን
ምስጋና ይሁን ስለ ክፉ ቀኖቻችን ክፉ ሆነብን ብለን ስለተከዝንባቸው ዕለታት ምስጋናን እንሰጣለን ስለ አለቀስንባቸው ቀናት ጠብቀን ፈልገን ስላጣናቸው ነገሮች ሁሉ ግዙፍ ምስጋናን ሠዋን የሠባውን መርጠን ገለባ ለሆንባቸው ቀኖቻችን መሰዋት አርገን በምስጋና አቀረብን ስለ አማርንበት ሳይሆን ትቢያን ስለተሸከምንበት ወቅት ስቡህ አልን ስለተፈለግንበት ዕለታት ሳይሆን ስለተገፋንበት ነውራችን በዝቶ ስለተገለጠት አለመፈለጋችንን ስለሰማንባቸው ሠአታት ቅፅበታት ሁሉ ንሴብሖ ላንተ በመጥቆር መጠልሸቶቻችን ውስጥ በምንዳክርበት ለዚች ሰአት ምስጋና ይሁን የልባችን እሳት ነፍሳችንን አየለበለበ ስላለበት ስላሁኗ ቅፅበት ይቺ ቅፅበት የተመሠገነች ትሁን የሞት ደጃፍን ስለቆረቆርንባት ስለዛች ቅፅበት አመሰገንን ክፉዎቼ ሆይ ምስጋናን ውሰዱ ነፍሴን አድን ዘን ይቅርታዬን ባቀብላችሁ ለገፋችሁ ለፈጠፈጣችሁ ለተጠየፋችሁ ዕልፉን ምስጋና ውሰዱ የይቅርታን ዕድሜ ለነፈጋችሁኝ ሁሉ ምስጋናዬ ከምድር አሸዋ በዝቶ በአብርሃም ቃል ኪዳን ያህል ሆኖ ይድረሳችሁ
ምስጋናን ለክፋት ክፋተቶቻችን ሁሉ እንሰዋለን
እናመሰግናለን

ሠብልዬን
ከደጃፋሽ ቆሜ በራፍሽን የመታሁ
አትምጣ እያልሽ ገስግሼ የመጣሁ
መኖር ቢያጓጓኝ ነው ሞቴንም ልሸሸው
ባንቺ በክንብንቤ ተከልዬ ያንን ህመም ላልፈው

ሠብልዬን
ደነዞዬዬ


@esubalew_sable
@esubalew_sable
@esubalew_sable
እናቴ ሆይ ጣምሽን አውቀዋለሁና አልተውሽም መጠጊያዬ ሆይ መከልያዬ ነሽና አልሸሽሽም መኖሪያም የለኝምና ካንቺ ውጪ አልሆንም
እንዲህ እናምናለን እንታመናለንም !!
አንዲት ቤተክርስቲያን
አንድ ሲኖዶስ
አንድ መንበር
አንድ ፓትርያርክ
.........
ባክሽ አንቺ አትራቂብኝ
እመብርሃን እናቴ ትንፋሽሽን እፋ በይብኝ
ፅናትሽን እፋ በይብኝ
ወይ ይቺን የሞት ፅዋ ጥላዋ ነፍሴን ካፈናት
እንዳልጠጣት አሳልፊያት
መራራ ክንፏን ገንጥለሽ ቀጠሮ ቃሏን ግደፊያት
አለዚያም ፅናቱን ስጪኝ ልጠጣው ኪዳነ ውሉን
የኔ ፍቃድ እምነትሽ ነው ያንቺ ፍቃድ ብቻ ይሁን ።
እንደ ጳውሎስ እንድፀና በፍርሃት እንዳልታሰር
በውስጤ ከሚታገለኝ በስጋ አውሬ እንዳልታወር
ለየዕለቱ ሞት እንዳልሰንፍ
የኪዳን ቃሌ እንዳይነጥፍ
ቃልሽ በህሊናዬ ዲብ ኃይልሽ በሕዋሴ ይረፍ ።
ፍርሃት ቢያረብብኝም አንቺ ካልሽኝ አልሰጋም
ኩርትም ብዬ እችልበት እሸሸግበት አይጠፋም
የግማደ መስቀሌን ጉጥ እታገስበት አላጣም
አለዚያ ብቻዬን ነኝ ኢትዮጵያ አላንቺ የላት
አንቺ አፅኝኝ እንድፀናላት ።
አስረጪብኝ የዕምነት ቀንጃ ለስጋቴ አጣማጅ አቻ
ለጭንቀቴ መቀነቻ ።
አዎን ብቻዬን ነኝ ፈራሁ
እሸሸግበት ጥግ አጣሁ
እምፀናበት ልብ አጣሁ.....

ሰቆቃወ ጴጥሮስ
ሎሬት ፀጋዬ ገ/ድህን
እሳት ወይ አበባ
ጥያቄ አለኝ

ሠው ለምን የየራሱን መኖር ከበደው ?
በሠው ኑሮ ገብቶ መበጥበጥስ መብት ነው? በምን ሕግስ ነው የሚዳኘው ፍትህስ አለው?
ኗሪውስ ከውስጡ በላይ ደጅ ያለውን ሠምቶ የካበውን መናድ በናደውም አብሮ የነበረውን መነደል መምታት ማሽሟጠጥ ማሸማቀቅስ አግባብ ነው የሠውነት ፍትሄስ የት ደረሰች ?
hope
AudioTrim
ስለ እናት pinned «ጥያቄ አለኝ ሠው ለምን የየራሱን መኖር ከበደው ? በሠው ኑሮ ገብቶ መበጥበጥስ መብት ነው? በምን ሕግስ ነው የሚዳኘው ፍትህስ አለው? ኗሪውስ ከውስጡ በላይ ደጅ ያለውን ሠምቶ የካበውን መናድ በናደውም አብሮ የነበረውን መነደል መምታት ማሽሟጠጥ ማሸማቀቅስ አግባብ ነው የሠውነት ፍትሄስ የት ደረሰች ?»
ጥያቄ አለኝ

ይህ የዘመን ክፍለ ጌዜ የኔና ያንተ አደል ? የኔና ያንተንስ መልክ አደል የሚይዘው ?
ታዲያ ምነው የኔ ያንተ ማንነት ክፉ ዘመንን መፍጠር አስመረጠው?
ምነዋ የዘመን ሃቃችንን ቀለማችንን አጠቆርነው ምነዋ?
ከሞት በኋላ ህይወት አለ !
ከመበስበስ በኋላም ማፍራት አለ !
ከመውደቅ በኋላም መነሳት አለ !
እያፈቀርን ነው ጥላቻን የምንሸምት
እየወደድን ነው በወደድነው ውስጥ የምንሻግት
የሻገተ ሁሉ መች ይጣላል ደርሶ
ሞቆ ወይ ደርቆ ይጎረሳል ተመልሶ ።

የማሞቁ ወይ የማድረቁ ባለን ነገር ቢወሰንም


ሠብልዬን
የዛሬዋን ፀሃይ ወደድናት አንቺን አሳይታናለችና እለቱንም ከፍ ከፍ አረግነው አንቺን በዚህ እለት አግኝተናልና ፍሪናዬ ሆይ እንወድሻለን ከፍ ከፍም አረግሻለሁ መስከረም በሆነ በስድስተኛው ወር ከቀንም በሶስተኛው አንቺን አግኝተናልና እንኳን ተወለድሽልኝ እንኳን በቸር ለአዲሱ አመትሽ ቸሩ አደረሰሽ ከማር የጣፈጠ ዘመንን ላንቺ ያርግ በዚህ እለት ለብዙዎቻችን ሙላት የሆነች ፍሬህይወት ተወለደች
በፀጋው ያኑርልን እድሜሽን ሳብ አርጎ ከመኖር ወለላው ያስጎንጭሽ የምድርን በረከት ያስታቅፍሽ
እንኳንም ተወለድሽ
አንቺን ለወለዱ ምስጋና አደረግን
ይልቅም ደሞ ለፈጠረሽ የገዘፈውን አቀረብን
🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂🎂


በረከቴ
ደሞ ከርሞ ያርገን አሜን

ሠብልዬን
በባዶነት ደጃፍ አለፍን ከምድር ህመም ቀመስን
ለመሙላት ተነሳን ሽንቁራችን ሠፍቶ መሙላታችን ከዳን

ሠብልዬን
ለልብ ዕረፍት የሚሰጥ ሰው አግኝቶ ይቺን ቁራሽ ህይወት በፍቅር ማስጌጥ ምንኛ ውብ ነው ።
ከዕለታት ባንዱ ቀን ልክ ካለመኖር እንደመጣን ሁሉ ወደ ህይወታችን የመጣ ሰው የምድር በረከት ሆኖልን የመኖር ጌጥ ባለ'ቤታችን ሲሆን ያለው ስሜት ጠርዝ አይገኝለትም ።
ሠው በምድር ሲኖር በፍቅር ነው ዘላለማዊነት ላይ ደርሶ አለመኖሩን አደብ የሚነሳው
ለሸራፋ ህይወት በሙሉነት የሚሳቀው በፍቅር ነው !
ናፍቀህ ሩብ ደቂቃ ውስጥ የመንፈቅ ያህል ስቆዝም ትዝታ ይሉት ነገር ውስጥ ሰምጠህ ለሌላ ትዝታ ነፍስህ ስትጣደፍ የቀጠርካትን ጥበቃ በሠከንድ ውስጥ አስሬ ስትንጎራደድ ልብህ ልትፈነዳ ስትደርስብህ ቅናት ይሉት ነገር ሲያደብንህ ምን ልበልህ.......
ቅናት የፍቅር ጥላው ይመስለኛል ፍቅር ካለ እሱ ወዴት ይቀራል ባፈቀርከው ላይ እንኳን የሠው አይን ዝናብ ባያርፍበት እፎይታህ በሆነ ።
በመኖር ፍቅር የተሳካለት እሱ የምድርን ገነቷን ያገኘ ነው!!

ሠብልዬን

https://www.tg-me.com/ስለ እናት/com.esubalew_sable
በየአመቱ አድዋን የግር ጉዞ እናረጋለን መነሻችን ዘነበወርቅ ታቦት ማደሪያ ሲሆን መተላለፊያችን በቶታል ጦርሃይሎች በፍርድቤት አብነት ተክለሃይማኖት መዳረሻችንም ፒያሳ ሚኒሊክ ሃውልት ስር ነው አብራችሁን ለመጓዝ ፍቃዳችሁ የሆነ ሁሉ ተጋብዛችኋል የፉከራና የሽለላውንም ልምምድ ከጀመርነው ቆየን ብትገኙ ደስታችን ነው ልታገኙን ከፈለጉ
0954944896 ይደውሉ
በውል ባንኖርም በውል እንድንሞት ይፈቀድልን!
እንዴት ነው ነገሩ ጎበዝ...በውል ባንኖር እንኳ በውል እንድንሞት ይፈቀድልና አሃ...ለዘመኑ የሚመጥን ኑሮና የተመጠነ ሃሳብ ባይኖረን እንኳ በዘመኑ በሽታ እንድንሞት ይፈቀድልን እንጂ..እንዲሁ ድፍት ቅርት አረ ደስ አይልም ...ላስታማሚም አስቸግረን በጠያቂ ጁስ ተጠግነን በደህና ቀን የማንጠጣውን በህመማችን አሳበን እንጨልጥበታ...በምን ሞተ? በስኳር ተመስገን የሃብታም በሽታ ነው የገደለው እንባልበት እንጂ ..እነ ግፊት ብዛት እነ ኩላሊት...አባላዘር ሣይደፍሩን እንዴት ቅጥ የለሽ በሆነ ግለሰባዊ ክርፋት ታውከን እንሙት እሱ ይሁን እነ ስኳር ግፊት ይቅሩ የተበከለ ምግብ በልተን  አተት ቢገለን ምን አለበት የተበከለ አስተሳሰብ በወጣንበት ከሚያስቀረን ተዉ ግን ተዉ ለዘመኑ የሚመጥን ሞት ይኑረን አርጅቶ መሞቱ ይቅር ባረጀ ሃሳብ እንዳንሞት ፍቀዱልን እንጂ አሃ ተውና..እንዴ ምርጥ ቢዝነስ ምን ይሆን ብለህ ራስህን ስታልፋ አንዱ ከመሃል የሞትና የሬሳ እቃ አቅራቢ መሆን...ልክ ብለሃል ወዳጄ ከኗሪው እንደሁ ባባራሪ ሟቹ በርክቷል...እናምልህ ምን ያረጋል የልብስ ሳጥን አልጋስ ምን አባቱ ምን ሊታለም ይተኛል ምን ያረጋል ወንበር በቅጡ ለማይቀመጡ ይልቅ ወዳጄ ሆይ የሬሳ ሳጥን ነው ምርጡ...አሁን አሁንማ fashion የተከተሉ ሳጥኖች መተውልሃል አምረህ ባትኖርም የለፋህበትን ኖረህ ባትበላውም ዘንጠህ ተቀበር እ እናሳ በባዶ ይመስልሃል ቀብር አስፈፃሚ ድርጅት መብዛቱ ይቀዘቅዛል አይቀዘቅዝም የለም ብቻ መቅበር ነው ውል አልባ ኑሮ ሲኖርህ ከመኖርህ ይልቅ በመሞትህ እርግጠኛ ስለሚኮንብህ ስለዛም ነው ትውልድን ከሚያበጅ የመፅሐፍ መሰደሪያ ይልቅ የሬሳ ሳጥን ቤት መብዛቱ ለዛም ነው የፍቅር ሳይሆን የሬሳ አበባ መሸጫ መበራከቱ/ፍቅርህን ቀድመህ ጥለሃላ ምን ያርጉህ/  ስለዚህም ነው እርቃንህን ለመሸፈን የሚበጅህ ልብስ ተትቶ የመገነዛ ጨርቅ ቤት መፈብረኪያ መበራከቱ ለዛ ነው ለመዳኛ ከሚሆንህ መዳኒት ይልቅ የሬሳ ማድረቂያ መድሃኒት መበርከቱ ከመኖርህ መሞትህ 100% እርግጥ ነውና የተመጣጠነ ኑሮ ሳይኖርህም ባልተመጣጠነ አሟሟት ትሸኛለህ አረ ጎበዝ አረ ጃሎ አረ ጎራው አሟሟታችንን መልሱን ለምን እንደ ፈሪ ከኋላ ከጀርባዬ መቀመጫዬን ብለህ ለመቀመጥ ትገለኝ ና እንደ ጀግና እንደ ደፋር ከፊቴ  ላልቃሽ ሙሾ ማሳመሪያም ግንባሬን መተህ በግንባር ግደለኝ ና ፊቴን እይ ፊትህን አሳይ ክብር ያለው ሞትን እንሟሟት ያኔ ምን አልባት ገዳይ ሟች ተገዳይም ደሞ ገዳይ ይሆን ይሆናል አልያማ ምስክር በሌለበት ፈሪም ጀብደኛ ነውና.......ውል ያለው ሞት ፍቀዱልን ወይ እግዜሩ ጠርቶን ወይ በሽታ ግትቶን እንሙትበታ ሞታችን ያለ ትርጉም አይሁንብን ወይ እንደ ጀብደኛ ታሪክ ላይጠራን በባዶ ታሪክ አይርሳን ....መኖራችንን ባታከብሩ አሟሟታችንን አሳምሩልና አቦ...በጨለመ እሳቤ ያልጨለምን እኛን አታጥቁሩን እኛ ምስራቅ የሆነ ልብ አለን የነገን ተስፋ ፀሃይን መውለጃ በናንተ ምዕራባዊ ልብ በጠለቀ ፀሃያቹ ዘመናችንን አታብሱብን በቃ እኛ ጎህ ነን ብርሃን የማለዳ ድባብ እናምላቹ ውል ያለው ኑሮ ኖረን ውል ያለው ሞት እንሙትበት ተውንንንንንንንንንን!!!

ሠብለወንጌል.... ሠብለ ...ሠብልዬን ....ሠብሊና

@esubalew_sable
@esubalew_sable
@esubalew_sable
2024/06/25 22:08:51
Back to Top
HTML Embed Code: